የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ በናትናኤል
please login or sign up for comment your question and you can post any thing you want in the sub categories
otber wise if you don't login you cant comment or post!!

የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ምክሮች!

Go down

የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ምክሮች! Empty የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ምክሮች!

ፖስት by Admin on Sun Feb 01, 2015 12:49 pm

የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር ጠቃሚ ምክሮች!
1.የኢንተርኔት አጠቃቀምን መመጠን
የተለያዩ መተግበሪያዎች/Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ በሚሆኑበትጊዜየተለያየ መጠን ያለው
ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፣
ለምሳሌ:- ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑምስልክዎ ላይ ጭነው የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መተግበር ይችላሉ፡
ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ> mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ > ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ያህል መጠን ያለው ኢንተርኔት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መመጠን ይችላሉ፡፡
2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት
ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ ያለርስዎ ፈቃድ እንዳይዘምኑበማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
3. ቪዲዮ ሙዚቃእና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ መመልከት/መጫወት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ
ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችንበቀጥታ ሲመለከቱ ወይም ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮዎችእና
ሙዚቃዎችከሆኑከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
በአንዳንድ አጋጣሚዎችከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ እና ሙዚቃንመምረጥ በጥራት ዝቅተኛ ከሆነ ተመሳሳይ ይዘት
ካለው ቪዲዮ እና ሙዚቃበሁለት እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
ለምሳሌ:- በሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube)ቪዲዮ እና ሙዚቃንእየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱንዝቅ በማድረግ
የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡ይህንን ለማድረግ:-
3.1. ስልክዎ ላይየዩቲዩብ/youtube/ መተግበሪያን ይክፈቱ
3.2. ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ
3.3. High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ /Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ
ማድረግ ይችላሉ፤
ያስተውሉ:
ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ(256kbps) የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜጋባይት የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፣
በተመሳሳይ ሁኔታቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ 1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነበሰዓት ከ10 እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ/Notification/ እንዳይልኩ ማድረግ እና ከጀርባ በኩል/Background/ ኢንተርኔት
እንዳይጠቀሙ ማገድ:-
አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም በውስጥ በኩል እርስዎ ሳያውቁ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፤
ለምሳሌ:- የተሻለ የመተግበሪያው/Application/ ስሪት ሲኖር ራሳቸውን ያዘምናሉ።
ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች/notifications/
እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ
ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡
የጫኗቸውን መተግበሪያዎች ማዘመን /አፕዴት ማድረግም ሆነመጠቀም ሲፈልጉ ብቻራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ አድርገው መጫን ይችላሉ፤በዚህ መንገድ እርስዎ ሳይፈቅዱ ስልክዎ በውስጥ በኩል ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ማድረግ ይችላሉ፡፡
5.የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት
አንዳንድ መተግበሪያዎች ባይጠቀሙባቸውም ስልክዎ ላይ በመጫናቸው ብቻ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ስለሚችሉ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎች በማጥፋት ወይም /Uninstall/ በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
6.ያልተላኩ መልዕክቶችን ማጥፋት
በስልክዎ ኢሜይል የሚልኩ ከሆነእና ያልተላከ መልዕክት ማስቀመጫ ሳጥን /outbox/ ውስጥ መልዕክት ካለዎት፣ የሞባይልዎን ኢንተርኔት በሚያበሩበት ጊዜመላክ ይፈልጉ እንደሆነለመጠየቅ ዝግጁ ስለሚሆኑኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ትላልቅ አባሪዎችን መልዕክቱ ላይ አይይዘው ከሆነ ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፤ ስለዚህ ያልተላኩ መልዕክቶች ውስጥ ያሉ መልዕክቶችን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡
7.የኢሜይል ሴቲንግ
በሞባይልዎ የኢሜይል አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ በምን ያህል የጊዜገደብ አዳዲስ ኢሜይሎች ሲገቡ እንደሚያሳውቅዎመወሰን ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ:- ሁልጊዜም አዲስ ኢሜይል ሲገባ ሊሆንይችላል፣ በየ10 ደቂቃው ወይም እርስዎ በወሰኑት ጊዜሊያደርጉት
ይችላሉ፡፡የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንለመመጠን ይህን ሴቲንግ መቀየር ከፈለጉ፤
7.1 የስልክዎ 'email' ላይ የሚጠቀሙትን የኢሜይል አይነት ይምረጡ ለምሳሌ (POP3, IMAP,
Exchange)
7.2 በመቀጠልም ቅደም ተከተሉን በመከተል፣ በምን ያህል ጊዜአዲስ ኢሜይል መግባቱን ማሳወቅ እንዳለበት
መወሰን ይችላሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህ አገልግሎቶች ኢንተርኔትዎን በከፈቱበት ወቅት ሁሉበውስጥ ከጀርባ/በኩል ኢንተርኔት ስለሚጠቀሙ ካልፈለጉት በሚከተለው ዘዴ ማጥፋት ይችላሉ፡፡
እንደ ስልክዎ አይነት በጥቂቱ ቢለያይም በአብዛኛዎቹስልኮች ላይ ሴቲንግ ውስጥ location ወይም location settingን በመምረጥ እና የመገኛ አካባቢዎ በዋይ ፋይ ብቻእንዲገኝ በመፍቀድ፤ የኢንተርኔት
አጠቃቀም መጠንዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
9.ከአገር ውጪሲሆኑየኢንተርኔት ሮሚንግን ማጥፋት
ሲም ካርድዎን ከአገር ውጪበሚሄዱበት ጊዜመጠቀም እንዲችሉ የሮሚንግ አገልግሎት ለማግኘት ከኢትዮ ቴሌኮም
ጋርውል ፈጽመውከሆነ የሞባይልኢንተርኔትን በማጥፋት ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ።
ይህን ለማድረግ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይተግብሩ።
ስልክዎ አንድሮይድ የሚጠቀም ከሆነ Settings ውስጥ > Wireless & Networks የሚለውን ይመርጣሉ> Mobile Networks ውስጥ በመግባት > Data Roaming የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመገደብ ይችላሉ፡፡
ስልክዎ አይፎን/ iPhone ከሆነ: Settings ውስጥ > General የሚለውን ይመርጣሉ ከዚያም> Network ውስጥ > Data Roaming የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመገደብ ይችላሉ፡፡
10.ዋይ ፋይ ሲጠቀሙየሞባይል ኢንተርኔትዎን ማጥፋት
የዋይ ፋይአገልግሎት በሚያገኙበትአጋጣሚሞባይል ኢተርኔትዎን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
11.ሆትሰፖት እና ቴዘሪንግ/ Hotspots and tethering/
የስልክዎን ኔትዎርክበሌላ መሳሪያ መጠቀም ከፈለጉ እና ስልክዎን እንደ ዋይ ፋይሆት ሰፖት አድርገውት ከሆነ
ወይም በዩ.ኤስ.ቢ ሚጠቀሙበት ከሆነ ያገናኟቸው መሳሪያዎች ለምሳሌ ኮምፒውተር ቢሆን ከፍተኛ ኢንተርኔት
ስለሚጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ሌሎች ሰዎችም የእርስዎን ስልክ ኔትዎርክ እንደዋይፋይ ሊጠቀሙበት
ስለሚችሉ የምስጢር ቁጥር በማስገባት መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
12.የሞባይል ኢንርኔትን ማጥፋት
ከላይከተገለጹት የጥንቃቄ ነጥቦች በተጨማሪ ኢንተርኔት መጠቀም በማይፈልጉበት ጊዜየሞባይልዎን የኢንተርኔት
በማጥፋት በአግባቡ ይጠቀሙ፡፡
©የኮምፒውተር እውቀትዎን ያሳድጉ

Admin
Admin

Posts : 63
Points : 185
Reputation : 1
Join date : 2015-02-01
Age : 20

http://ethiopiantech.amharicforum.com

ወደ ላይ ውጣ Go down

ወደ ላይ ውጣ


 
Permissions in this forum:
በዚህ መድረክ ለጉዳዮች መልስ ፖሰት ማድረግ ይችላሉ ጉዳዮች ምላሸ መስጠት አይችሉም