የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂ በናትናኤል
please login or sign up for comment your question and you can post any thing you want in the sub categories
otber wise if you don't login you cant comment or post!!

ለሞባይል ሸመታ ወሳኝ ነጥቦች…

Go down

ለሞባይል ሸመታ ወሳኝ ነጥቦች… Empty ለሞባይል ሸመታ ወሳኝ ነጥቦች…

ፖስት by Admin on Sun Feb 01, 2015 1:27 pm

ለሞባይል ሸመታ ወሳኝ ነጥቦች…
ብዙ ጊዜ ሞባይል ስንገዛ የምንገዛውን ሞባይል ጥራት ለመለየት ስለምንቸገር በቅርብ ያገኘነውን ሰው በመጠየቅ በምስክርነት እንወስናለን ፡፡
የስሞች መብዛትም አንዱ ችግር ነው፡፡ሳምሰንግ ፣ኖኪያ፣ ኤልጂ፣አፕል፣ወዘተ ወዘተ እየተባለ ይሄ ያ ይበልጣል ሙግትም አለ፡፡ እስቲ ለዛሬ ከሞባይል ቀፎ መሰረታዊ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ፡፡
የመጀመሪያው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ አንድሮይድን ና ቴክኖ አንድሮይድን ይጠቀማሉ እንበል፡፡ ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ መሆኑ በሞባይል ቀፎዎች መሀል ያለውን ያገልግሎት ጥራት፣ ከዘመነው (አፕዴት ቴክ ) ጋር ያለውን መግባባትና ችሎታ፣ለቫይረስ ያለመጋለጥ ብቃትን ጨምሮ ከከባድ ድረ ገጽና አፕሊኬሽን ጋር ተጣጥሞ የመስራት አቅሙን ማሳየቱ ጥቂቶቹ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡
ባጠቃላይ የሞባይል ቀፎን ባሕርይ ወሳኝ ምዕራፍ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው፡፡ ከሞባይል ቀፎ አንፃር አንድሮይድ ባሁኑ ወቅት ከዊንዶው እና ማክ የተሻለ የኪስን አቅም ባማከለ መልኩ ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡
ሁለተኛው ማነፃፀሪያ ደግሞ ዋይ ፋይ፣ ብሉቱዝ፣ ዩኤስቢ፣ ጂፒኤስ፣፣ ቱጂ፣ ስሪጂ፣ ፎር ጂ የመሳሰሉትን መያዙና በተጨማሪም ሁለትና ከዚያ በላይ ሲም መቀበሉ ሲሆን ከዚህም በላይ ኖርማል ሲም ጂ ኤስ ኤም እና ruim (cdma sim ) ባንድ ላይ መያዙ ነው፡፡
የፋይል አደረጃጀት ስርአታቸው ለአጠቃቀም ቀላል መሆንና እንደፈለግነው መቀየር መቻሉና ምቹ መሆናቸው ደግሞ ሌላው መለኪያ ነው ፡፡ ለምሳሌ ተች ስክሪን፣ ስክሪን ጋድጌትስን መቀይር መቻሉና በፋይል ማናጀር በምንፈልገው መንገድ መቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ‘እንደዚህ ሁንልኝ’ ስንለው የሚሆንልን ስማርት ፎን ደስ አይልም ?
ሶሰተኛው ማነፃፀሪያ የራሱ የሞባይሉ ሜሞሪ ( ፎን ወይም ኢንተርናል ሜሞሪ) ምንለው ነው፡፡ ይህ ሜሞሪ አቅሙ በጨመረ ቁጥር ዋጋውም አብሮ መጨመሩ እሙን ሲሆን ለቀፎዎች የዋጋ ልዩነት መሰረትም አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ቀፎዎች የምንከትላቸውን የውጭ ሜሞሪዎችና አብሮአቸው የተሰራውን ሜሞሪ ባንድ አይነት ስለማይጠቀሙ በፍጥነት፣ በጥራትና በአቅማቸው ላይ የሚያመጣው ልዩነት ትልቅ ነው፡፡ ቀፎዎች (TIF card)ቲፍ ካርድና ኤስዲ(SD card) ካርድን(ሞባይላችን ላይ ምንከታቸው ሜሞሪዎች ማለቴ ነው) ሲጠቀሙ ፍጥነታቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የሚጭኑት አፕሊኬሽን ውስንና ቀጥታ ፍሰት (Real Time access) ነው፡፡ ስለዚህ ቀፎ ስንገዛ የራሱን ሜሞሪ አቅም ማስተዋል ግድ ይላል፡፡
አራተኛው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ‘ፎን ክሎክ’ የሞባይል ቀፎውን ሲስተም ሃርድዌር ፍጥነት ሚወስን ነው።ለምሳሌ ድረ ገፅ ላይ አንድ ሞባይል ያለምንም መቆራረጥ ከዩቱብ ወይንም ከኛው ድሬትዩባችን ላይ ቪዲዮ ቢያጫውት የክሎክ ፍጥነቱንና የቢዩልት ኢን ሜሞሪን(phone memory) ጥራት ያሳያል፡፡
በተጨማሪ ቪዲዮ ኮሊንግ ያለችግርና (ፍሪዝ) በእስካይፒ መጠቀም ከቻልን በርግጥም የቀፎዎችን ግሩም ጥራት ያሳየናል፡፡ እዚህ ጋር ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባልኝ ምፈልገው አሁን ያለው የአገራችን የኔትዎርክ ችግር በቀፎው እንዳይሳበብ የኔትዎርኩን ሁኔታም ማየት መልካም መሆኑን ነው፡፡
አምስተኛ የባትሪ ጥራትና ቆይታ ነው ፡፡ አንዳንድ ሞባይሎች ባትሪ ሙጥጥ አያረጉ ‘‘እረ የቻርጀር ያለህ!’’ እያሰኙ ስንቱን አስጨንቀዋል፡፡ በርግጥ የሞባይል አቅምና ያገልግሎት ጥራት በጨመረ ቁጥር ባትሪ አጠቃቀምም አብሮ ቢጨምርም ብዙ ሞባይል አምራቾች የሞባይል ባትሪ ጥራትን በማሻሻል እነዚህ ቀፎዎች ለ18 ሰኣት አንዲያገለግሉ አርገው ሰርተውልናል፡፡
ሌላው ባትሪን በተመለከተ ማየት ያለብን የተሻለ ሞባይል ለመግዛት የባትሪ ማኔጅመንት ፕሮቶኮል አውቶማቲክና ማኑዋል አማራጭ እንዳለው ማጣራት ነው፡፡
የባትሪ ቀበኛ ከሆኑት ስክሪን ብራይትነስና ቫይብሬት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከጀርባ ሳናያቸው የሚስሩ አፕሊኬሽኖች መኖር፣ ቫይረስና አንቲ ቫይረስ ማኔጅ ማድረግና የመሳሰሉትን መቆጣጠሪያ ሶፍት ዌር መጫን የባትሪን ቀይታ ለማራዘም የምጠቁመው ተጨማሪ መፍተሄ ነው።
በመጨረሻም የተሻለ ሞባይል ለመያዝ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ኢሜይል፣የጽሑፍ መልዕክት፣ካሜራ ጥራት፣ ምቾት፣ሰክሪን ስፋትና የተመረተበትን ቀን ማረጋገጡ ጠቃሚ ነው፡፡
ቸር ይግጠመን፡፡

Admin
Admin

Posts : 63
Points : 185
Reputation : 1
Join date : 2015-02-01
Age : 20

http://ethiopiantech.amharicforum.com

ወደ ላይ ውጣ Go down

ወደ ላይ ውጣ


 
Permissions in this forum:
በዚህ መድረክ ለጉዳዮች መልስ ፖሰት ማድረግ ይችላሉ ጉዳዮች ምላሸ መስጠት አይችሉም